በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክሪስትያን - ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ሀገረ ስብከቱ
  • ቅዱሳት መካናት
  • አገልግሎቶች
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ምግባረ ሠናይ
  • ሰንበት ት/ቤት
  • አብነት ት/ቤቶች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

“ባለሙያዎች የዕውቀት አሥራት በማበርከት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ አእምሯዊ አሻራችሁን አስቀምጡ” ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ (የክብር ዶ/ር)

June 10, 2023
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በመንበረ ጵጵስናቸው ከሀገረ ስብከቱ የሙያ ድጋፍ አገልግሎት ሕብረት የየክፍል ተጠሪዎች ጋር ምክክር ባደረጉበት ወቅት የዕውቀት አሥራት የማበርከት ጅምር በጎ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አባታዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።
አባቶቻችን ያቆዩልን ስንዱ እመቤት የሆነች ቤተ ክርስቲያን ቀጣይ እንዲትሆን በየሙያችሁ በማገዝ መዋቅሩን ማዘመን ይጠበቃል ብለዋል ብፁዕነታቸው።
ዓባይን ዓባይ ያሰኘው ገባሮቹ ናቸው ያሉት ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የቤተ ክርስቲያኗ መዋቅር ጠንካራ ሊሆን የሚችለው ማኅበራት፣ ምሁራንና ምእመናን ከካህናት ጋር በቅንጅትና በመናበብ ሥንሠራ ነው ብለዋል።
የሙያ ድጋፍ አገልግሎት ኅብረቱም አቅማቸው በፈቀደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእውቀት፣ በጉልበትና በገንዘብ ለማገልገል ቃል ገብተዋል።
የሙያ ድጋፍ አገልግሎት ኅብረቱ የምህንድስና፣ የጤና፣ የሕግ፣ ሥራ አመራርና ምጣኔ ሀብት፣ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ፣ ቱሪዝም ልማትና ቅርስ ጥበቃ፣ ጥናትና ምርምር፣ ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት እንዲሁም የሚዲያ ዘርፎችን ያካተተ ኮሚቴ በብፁዕነታቸው ተቋቁሞ ሀገረ ስብከቱን በሙያ እያገዘ ይገኛል።
የምክክር ጉባዔው ብፁዕነታቸው የቀጣይ የሥራ መመሪያ ሰጥተው በቃለ ምእዳንና ቡራኬ ተጠናቋል።
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል ሦስት)
  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል ኹለት)
  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል አንድ)
  • ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ነው። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ)
  • በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

Archives

  • June 2025
  • May 2025
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
© በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን - የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት | በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
  • Link to Facebook
Link to: በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት ንዑስ (የቀጠና ጽ/ቤት) እና የስብከተ ወንጌል አዳራሽ አስገንብቶ አስመረቀ። Link to: በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት ንዑስ (የቀጠና ጽ/ቤት) እና የስብከተ ወንጌል አዳራሽ አስገንብቶ አስመረቀ። በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት... Link to: በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። Link to: በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top