በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክሪስትያን - ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ሀገረ ስብከቱ
  • ቅዱሳት መካናት
  • አገልግሎቶች
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ምግባረ ሠናይ
  • ሰንበት ት/ቤት
  • አብነት ት/ቤቶች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ነው። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ)

June 15, 2023

ሰኔ 7 ቀን 2015 ዓ.ም (ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት) በበጎ አድራጊ ባለሞያዎች የተዘጋጀው የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ድረገጽ በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ቡራኬ ትናንት ሰኔ 6 ቀን 2015 ዓ.ም ሥራ ጀምሯል። ድረገጹ (https://eotc-nw.org ) የሀገረ ስብከቱን መሠረታዊ መረጃዎች፣ ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎች ስልታዊ ይዘቶችን ለህዝበ ክርስቲያኑ ለማድረስ ታልሞ የተሠራ ነው።
ድረገጹ በአጥቢያ ዶት ኮም (atbiya.com) በነጻ ተዘጋጅቶ ለሀገረ ስብከቱ ተበርክቷል።

ቤተ ክርስቲያኗ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለመስጠት የባለሞያዎች እገዛ ወሳኝ በመሆኑ በሌሎች መስኮችም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ብፁዕነታቸው አጽንዖት ሰጥተው አባታዊ መመሪያ አስተላልተዋል።

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ፍሥሐ ጌታነህ በበኩላቸው ሀገረ ስብከቱ የበርካታ ታሪካዊና መንፈሳዊ ቅርሶች መገኛ ከመሆኑ ባሻገር በአንጋፋው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ እና በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ አባታዊ መሪነት ሰፊ ሰብዓዊና ቁሳዊ የልማት ሥራዎች እየተስፋፉበት መሆኑን ገልፀዋል። ሀገረ ስብከቱ ያለውን ሀብት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ታግዞ ለማስተዋወቅና ለማልማት በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይልና ግብዓት ለማሟላትም ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ባለሙያዎች ቤተ ክርስቲያኗን በእውቀታቸውና በሞያቸው እንዲያገለግሏት ሀገረ ስብከቱ የባለሞያዎች ኅብረት አቋቁሞ እየሠራ መሆኑንም ጠቁመዋል።  ድረገጹን ያበለፀጉት ባለሞያዎች ከሀገር ውጭና በሀገር ውስጥ የሚገኙ ሲሆን በቀጣይ በስልጠና እና በሌሎች ጉዳዮች ያልተቆጠበ ድጋፍ ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-nw.org/a/wp-content/uploads/atbiya-emblem-400-with-space.png 400 400 tc https://eotc-nw.org/a/wp-content/uploads/eotc-nw-logo-2.png tc2023-06-15 06:59:002023-06-15 07:04:12ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ነው። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ)
Search Search

Recent Posts

  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል ሦስት)
  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል ኹለት)
  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል አንድ)
  • ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ነው። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ)
  • በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

Archives

  • June 2025
  • May 2025
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
© በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን - የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት | በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
  • Link to Facebook
Link to: በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። Link to: በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ። በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ... Link to: ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል አንድ) Link to: ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል አንድ) ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top