በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክሪስትያን - ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ሀገረ ስብከቱ
  • ቅዱሳት መካናት
  • አገልግሎቶች
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ምግባረ ሠናይ
  • ሰንበት ት/ቤት
  • አብነት ት/ቤቶች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

June 10, 2023
ከላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ጽ/ቤት ቅዱስ ላሊበላ ከተማ በስተ ምሥራቅ 65 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በ017 ቀበሌ እንጃፋት ከተማ የሚገኘው የአፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት በብፁዕ አቡነ ቄርሎስና በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የሀገረ ስብከታችን ሊቃነ ጳጳሳት ተባርኮ በሀገረ ስብከቱ ልዑካን የመሠረት ድንጋይ ተቀምጧል፡፡ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑን በካናዳ ቶሮንቶ ነዋሪ የሆኑት ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታደሰ የንሥሓ ልጆቻቸውን በማስተባበር ከሰበካው ካህናትና ምእመናን ጋር ለመገንባት ዝግጅት በማድረግና በመወሰን የመሠረት ድንጋዩ እንዲቀመጥ ተደረጓል።
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የገዳማትና ቅርስ ክፍል ኀላፊ አባ ኀይለገብርኤል ፍሥሓ፣ የሀገረ ስብከቱ ቁጥጥር ክፍል ኀላፊ ሊቀ ትጉሃን አደባባይ ሰፊው፣ የላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ካህናት ይሄይስ ተመስገን፣ የወረዳው ቤተ ክህነት የሥራ ኀላፊዎችና ሠራተኞች፣ የአፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል አገልጋይ ካህናትና ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት ማክሰኞ ግንቦት 22 ቀን 2015 ዓ.ም ሥርዐተ ጸሎት በማድረስ የመሠረት ድንጋዩ ተቀምጧል።
ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታደሰ በላስታ፣ በግዳን፣ በዋግ ኽምራ ልዩ ዞን ጋዝጊብላ ወረዳዎች ከ36 በላይ አብያተ ክርስቲያናትን ንሥሓ ልጆቻቸውን በማስተባበር አሠርተው ንዋየ ቅድሳት በመርዳት ቤተ ክርስቲያንን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
Search Search

Recent Posts

  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል ሦስት)
  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል ኹለት)
  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል አንድ)
  • ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ነው። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ)
  • በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

Archives

  • June 2025
  • May 2025
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
© በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን - የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት | በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
  • Link to Facebook
Link to: “ባለሙያዎች የዕውቀት አሥራት በማበርከት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ አእምሯዊ አሻራችሁን አስቀምጡ” ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ (የክብር ዶ/ር) Link to: “ባለሙያዎች የዕውቀት አሥራት በማበርከት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ አእምሯዊ አሻራችሁን አስቀምጡ” ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ (የክብር ዶ/ር) “ባለሙያዎች የዕውቀት አሥራት በማበርከት ለቅድስት... Link to: ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ነው። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ) Link to: ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ነው። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ) ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በዘመናዊ...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top