በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክሪስትያን - ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ሀገረ ስብከቱ
  • ቅዱሳት መካናት
  • አገልግሎቶች
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ምግባረ ሠናይ
  • ሰንበት ት/ቤት
  • አብነት ት/ቤቶች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

የልማት እንቅስቃሴዎች

May 9, 2023

የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት አንጋፋ ከሚባሉት ሀገረ ስብከቶች አንዱ ሲሆን ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ከ1980 ዓ.ም ጀምሮ ዋግኸምራን ጨምሮ በእግር እና በበቅሎ እየተንቀሳቀሱ በርካታ መንፈሳዊና ቁሳዊ ልማት አስፋፍተዋል፡፡

  • በደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ዓለም አቀፍ ጎብኝዎችን ታሳቢ ያደረጉ የእንግዶች ማረፊያ ሆቴሎች፣ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ለሚያገለግሉ ሊቃውንት ድጎማ የሚውል የገቢ ማስገኛ ሁለገብ ሕንፃ ወልድያ ከተማ ላይ ተገንብቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
  • አሁንም በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የልማት ሥራው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መመሪያ ሰጭነትና በሀገረ ስብከቱ የገንዘብ ድጋፍ ጭምር ኹሉም ወረዳ ቤተ ክህነቶች የሚሰጡትን መንፈሳዊ አገልግሎት ለማጠናከር በወረዳ ዋና ከተሞች የገቢ ማስገኛ ሕንፃዎችን ገንብተው ገቢ ማመንጨት ጀምረዋል፡፡
  • የአብነት ትምህርት ቤቶችን በዘመናዊ መንገድ በማደራጀት ሙሉ ጊዜያቸውን ለትምህርታቸው እንዲያውሉ ታስቦ በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ ከመሆናቸው በፊት የጀመሩትና አሁን ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ ማስተማር የጀመረው የአስፋ ገነተ ጽጌ ፈለገ አእምሮ መንፈሳዊ ት/ቤትና 300 ወንዶችና 100 ሶቶችን ተቀብሎ ለማስተማር ታስቦ የሚገነባው የወልድያ ምሥራቀ ፀሐይ ወይብላ ቅድስት ማርያም አዳሪ መንፈሳዊ ት/ቤት ይገኙበታል፡፡
  • በሀገረ ስብከቱ የ10 ዓመት መሪ እቅድ መሠረት በሀገረ ስብከቱ አስራ አራቱም ወረዳዎች አንድአንድ በዘመናዊ መንገድ የተደራጁ የአብነት ት/ቤት እንዲገነቡ የቦታ ርክክብና የመሠረት ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነስርዓት ተካሂዷል፡፡
    በዘመናዊ ትምህርት ትውልዱን አንጾና ቀርፆ ለማሳደግ ሀገረ ስብከቱ አንድ አጸደ ሕፃናትና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ያለው ሲሆን በአድባራትም በርካታ ት/ቤቶች እየተከፈቱ ነው፡፡
Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-nw.org/a/wp-content/uploads/eotc-nw-logo-2.png 0 0 tc https://eotc-nw.org/a/wp-content/uploads/eotc-nw-logo-2.png tc2023-05-09 08:06:042023-05-09 08:07:42የልማት እንቅስቃሴዎች
Search Search

Recent Posts

  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል ሦስት)
  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል ኹለት)
  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል አንድ)
  • ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ነው። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ)
  • በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

Archives

  • June 2025
  • May 2025
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
© በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን - የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት | በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
  • Link to Facebook
Link to: ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ Link to: ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ Link to: በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት ንዑስ (የቀጠና ጽ/ቤት) እና የስብከተ ወንጌል አዳራሽ አስገንብቶ አስመረቀ። Link to: በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት ንዑስ (የቀጠና ጽ/ቤት) እና የስብከተ ወንጌል አዳራሽ አስገንብቶ አስመረቀ። በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት የላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት...
Scroll to top Scroll to top Scroll to top