በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክሪስትያን - ሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት
  • ቀዳሚ ገጽ
  • ስለ ሀገረ ስብከቱ
  • ቅዱሳት መካናት
  • አገልግሎቶች
    • የልማት እንቅስቃሴዎች
    • ሐዋርያዊ ተልእኮ
    • ምግባረ ሠናይ
  • ሰንበት ት/ቤት
  • አብነት ት/ቤቶች
  • ያግኙን
  • Menu Menu

አብነት ትምህርት ቤቶች የቤተ ክርስቲያናችን የህልውናዋ እስትንፋሶች ናቸው፡፡

April 27, 2023

በሀገራችን የማዕከላዊ መንግሥት ምስረታ ጉልህ ሚና የነበራት ቤተ ክርስቲያናችን ፊደል ቀርጻ፣ ብራና ፍቃና ቀለም በጥብጣ ዜጎችን ያስተማረች ቀዳማዊ ትምህርት ሚኒስቴር እንደነበረች የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡

በብፁዕ_አቡነ_ኤርምያስ አስተባባሪነት በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በወልድያ ምስራቀ ፀሐይ ወይብላ ማርያም እየተገነባ ያለው መንፈሳዊ አዳሪ ትምህርት ቤት፤ በአገልጋይ እጥረት የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፈቱ፣ ምዕመናንን አስተምረው ለንስሐ የሚያበቁ፣ ቀድሰው የሚያቆርቡ ማህሌታውያን በዕውቀት የተሞሉ ካህናትን ለማፍራት እና የነገዋን ቤተክርስቲያን ለማስቀጠል ዘላቂ ዓላማ ይዞ እየተገነባ ይገኛል።

ይህ የአብነት ትምህርት ቤት በ 22 ሺህ ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 7 ሺህ ካ.ሜ የቤተክርስቲያኗ ይዞታ እና የከተማ አስተዳደሩ 15 ሺህ ካሜ በመፍቀድ ለዚህም ለተነሺ ባለ ይዞታዎች ሀገረ ስብከቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ በመክፈል የግንባታ ሥራው እየተካሄደ ነው፡፡

ግንባታው ሲጠናቀቅ በአንድ ጊዜ በኹሉም የጉባኤ ቤቶች 300 ወንድ እና 100 ሴት በጠቅላላ 400 ተማሪዎችን በመቀበል ሊቃውንትን የሚያፈራ ነው፡፡

Share this entry
  • Share on Facebook
  • Share on X
  • Share on WhatsApp
  • Share on Pinterest
  • Share on LinkedIn
  • Share on Tumblr
  • Share on Vk
  • Share on Reddit
  • Share by Mail
https://eotc-nw.org/a/wp-content/uploads/favicon.png 169 151 tc https://eotc-nw.org/a/wp-content/uploads/eotc-nw-logo-2.png tc2023-04-27 16:55:342025-06-30 11:24:45አብነት ትምህርት ቤቶች የቤተ ክርስቲያናችን የህልውናዋ እስትንፋሶች ናቸው፡፡
Search Search

Recent Posts

  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል ሦስት)
  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል ኹለት)
  • ዐይንና ጆሮ የሚያሻው፣ የቅዱሱ ዐይንና ጆሮ (ክፍል አንድ)
  • ሀገረ ስብከቱ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ለምእመናን ተደራሽ ለማድረግ እየሠራ ነው። (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ)
  • በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት የእንጃፋት አፄ አምባ ቅዱስ ገብርኤል ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

Archives

  • June 2025
  • May 2025
  • June 2023
  • May 2023
  • April 2023
© በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን - የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት | በአጥቢያ ዶት ኮም የተሰራ
  • Link to Facebook
Link to: የሰንበት ት/ቤት Link to: የሰንበት ት/ቤት የሰንበት ት/ቤት Link to: ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ Link to: ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ
Scroll to top Scroll to top Scroll to top